Thursday, October 10, 2013

















የልቤን አዳራሽ መኖርያ አርጋዋለች!
ያልወለዳቹ ውለዱ.የተጣላቹ ተዋደዱ
ጉዞ ላይ ያላቹ ይቅናቹ መንገዱ
ከምንም በላይ ግን አደራ ይችን ልጅ &  እናቶቻችሁን ውደዱ!!!

Sunday, July 21, 2013

አንቺና መንግስቴን እንዲህ ምወዳቹ ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ

አባትሽ ጀነራል ወንድምሽ ሻለቃ
እናትሽም ዳኛ እህትሽ ጠበቃ
ታዲያ እንዴት ብዬ ልጥላሽ ለደቂቃ
በዚህ ሁሉ ጉልበት ተከበሽ እያየው
እኔስ ምን አቅብጦኝ አንቺን አጠላለው
ደግሜ ደግሜ ውዴ እወድሻለው
አዎ እወድሻለው
"እልፍ አህላፍ ለሊት
ሚሊዮን መሠለኝ
እኔ አንቺን ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ"
የሚለውን ግጥም
ሁሌ ማነብልሽ
ለምን እንደሆነ
አድምጪኝ ልንገርሽ
ውዴ.........
አንቺና መንግስቴን
እንዲህ ምወዳቹ
ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ

Tuesday, July 2, 2013

ሙያዊ የፍቅር ደብዳቤ



ውበትሽ አይኔን double click አድርጎ Enter ብሎ ልቤ
ውስጥ ከገባ ሰነባብቷል : :
ውዴ ሆይ ዛሬም ድረስ የስሜቴን keyboard የሚነካካው
ትዝታዬ መልክሽን screen saver በማድረግ ልቤ Save
አድርጎ ይዞሻል : : የኔ ፍቅር ሀያሉ ናፍቆትሽ Monitorን
አቃጥሎ ከማበዴ በፊት ውስጤ ለተፈጠረው ቅናት ማምከኛ
የሚሆን Antivirus እንዲሆን የብዕርሽን ቪዝዋል ግዕዝ ላይ
አድርጊና ደብዳቤ Type አድርገሽ ላኪልኝ...
ደግሞ አንዷን ለመጥበስ የኔን ደብዳቤ Copy አድርጉና Delet
ነው ማደርጋቹ ወንዶች ሰምታቹዋል......

One love Ethiopia.


መሄዴ ነው



ባር ባር አለው ሆዴ ልቤ መሬት ለቆ
ሊያከንፈኝ እንዳይሆን አለግብሩ መጥቆ
አለአስተዳደጉ አለባህሉ ወድቆ
ሽው እልም ሽው እልም ልቤ ወፌ ይላላ
በመስተፋቅር ቀስት በሮሮ ምህላ
እንደደመና አክናፍ እንደጮራው ጥላ
ሽው እልም ሽው እልም ሽው እልም ይላላ
ነሸጠው ሸፈጠ ሄደ ሸመጠጠ
በመስተፋቅር ቀስት በሮሮ አመለጠ።


ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን