አንቺና መንግስቴን እንዲህ ምወዳቹ ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ
አባትሽ ጀነራል ወንድምሽ ሻለቃ
እናትሽም ዳኛ እህትሽ ጠበቃ
ታዲያ እንዴት ብዬ ልጥላሽ ለደቂቃ
በዚህ ሁሉ ጉልበት ተከበሽ እያየው
እኔስ ምን አቅብጦኝ አንቺን አጠላለው
ደግሜ ደግሜ ውዴ እወድሻለው
አዎ እወድሻለው
"እልፍ አህላፍ ለሊት
ሚሊዮን መሠለኝ
እኔ አንቺን ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ"
የሚለውን ግጥም
ሁሌ ማነብልሽ
ለምን እንደሆነ
አድምጪኝ ልንገርሽ
ውዴ.........
አንቺና መንግስቴን
እንዲህ ምወዳቹ
ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ
No comments:
Post a Comment