Monday, April 29, 2013

የፍቅር ጥግ
------
የሰርጋቸው ለት...
የመውደዱን ስፋት የማፍቀሩን ጣርያ
እንዲህ ሲል ነገራት በውብ ቃል ማብራርያ
ባንቺ ቢመጡብኝ ምድር ላይ እያለሁ
እንኳን ከሰው ቀርቶ ከእግዜር እጣላለሁ
አላት፣ አወሩ ፍቅር ደሰኮሩ
ኋላ ግን በወሩ በጣም ተቃቃሩ
ከወዳዳት በላይ ከፊት ይልቅ ጠላት
በስተመጨረሻ አናዳው መሰለኝ
እራሱ ገደላት፡፡
-------
(አብርሃም ሥዩም፤ ደም መላሽ)
ይስጥሽ

እቴ
ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከፀጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ፀጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከዓይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ ዓይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።

ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም

እንዴት እሞታለው
ያላንቺ እንደ ማልኖር ልቤ እያወከው
እንደዚህ እያልኩኝ ራሴን አሞኛለው
ያላንቺ አልኖርም አፈር እሆናለው
ከጎኔ አትራኪ ስቸነቅ ውላለው
ካይኔ አትጥፊ እኔ ምን ይውጠኛል
እያልኩኝ መኖሬ ዛሬ ይኮቸኛል
ምንም አልሆንኩኝም አንቺን በማታቴ
ምንም አልጎደለኝ አልተዘጋም ቤቴ
ሰውነቴን ይዜ ልቤን ሰተቼ
እንዴት እሞታለው 1 ሰው አትቼ
በሌላ ብታዪው እኔ አንቺን ማፍከሬ
እኔ ግን አልሞትኩመ አለው እስከዛሬ
መካብሬ የታል የታለስ አፈሬ
እኔንም ገርሞኛል በሂወት መኖሬ
/ጌትነት ዳኒኤል/

~ውዴ~Aster
'ከእኔና ከእናት
ማን ይበልጥብሀል'
ብለሽ ለምትይኝ
አሰልቺ ጥያቄ
አንቺሻ ነሻ ውዴ
እላለው አውቄ
ግን......
እኔም በተራዬ
ልጠይቅሽ አንዴ
ከእናትም በላይ ነሽ
ብዬ ሳወራልሽ
ታምኚኛለሽ እንዴ????
ካላንቺ አልኖርም aster
ሰማይ ምድር ቢሆን ነገር ቢገለበጥ
ሴት ወንድ ሆና ወንድ ፀንሶ ቢያምጥ
ማበጠሪያ ገዝቶ ቢሰጥ ለመላጣ
ልጅ በተራው አባቱን ቢቆጣ
ነጭ ጋዎን ለበሶ ሒወትን ለማዳን
ፊዚክስን አጥንቶ እንደው ዶክተር ቢኮን
ሞተን ብንነሳ ቢታየን በማታ
እግር እጅ ሆኖ እጅ በእግር ቦታ
እንኳን ሰው እንስሳ ተራራም ቢሰደድ
ወዳጅ ጠላት ቢሆን እሳት በውሀ ውስጥ ቢነድ
ይሔን ግን አውቃለው ማንከይረው መቼም
አንቸቺም ካለኔ እኔም ያላንቺ አልኖርም
/ጌትነት ዳኒኤል/ hell/
የእረኛው የፍቅር ቃላት
ሳገኝሽ-
ላሜ ጠፍታ ሳገኛት እንደሚሰማኝ አይነት ስሜት፣
ስትስቂልኝ-
ከብቶቼ በልተው ሲጠግቡ እንደሚሰማኝ አይነት ሃሴት፣
ስታኮርፊ-
በሬዬን ዋዥማ የነፋው ያህል ይጨንቀኛል፣
እይዘው፣
እጨብጠው፣
የማደርገው ይጠፋኛል።
***
አደራሽ በንግግሬ በምሳሌዬ አትሳቂ፣
የፍቅሬን ጽናት ለማውቅ ከፈለግሽ ከብት ጠብቂ።

ዋዥማ ማለት የላሞችን ሆድ ቅብትት አድርጎ ነፍቶ እስከሞት የሚያደርስ ችግር ይፈጥራል ተብሎ በተለምዶ የሚወሰድ የሳር አይነት ነው።


Tuesday, April 23, 2013


የፍቅር ዓይነቶች” (types of Love)
/1/ “ሮማንቲክ ላቭ” /Romantic Love/
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ሄሮድስ ነው።
ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት
ሄሮድያዳን ያፈቀራት ስትደንስ አይቷትና ዳንሷም
ስለማረከው ብቻ ነው። ይህ ዓይነቱ ፍቅር
“ሄሮድሳዊ ፍቅር” ይባላል። ይሄኛው የፍቅር
ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን
ቅርጽ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው።
ሌሎች መሰረታዊ ነገሮችን ለምሳሌ ሃይማኖት ፣
ባሕርይ ፣ አስተሳሰብ ወዘተ ተረፈዎችን ከቁም
ነገር አይቆጥሩትም። ሮማንቲክ አፍቃሪዎች
ብዙን ጊዜ ቀናተኛ ናቸው። ያፈቀሩት ሰው
ከማንኛውም ሰው ጋ እንዲያዩት አይፈልጉም።
/2/ “ፓሽኔት
ላቭ” passionate Love
ስሜታዊ ፍቅር! ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር
ነው። ስሜታዊ ፍቅር passionate Love
በጣም አስቸጋሪ የፍቅር አይነት ነው። ሕሊናን
ረፍት ከመንሳቱ በላይ ሕይወትን
የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ
አለው። ለምሳሌ ትምርትና ስራ መጥላት ፣
የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት
ይገኙበታል። ስሜታዊ ፍቅር የሚቆየው ስሜቱ
እስኪሳካ ሩካቤ ሥጋ እስኪፈፅም ድረስ ብቻ
ነው። ከዚያ በኋላ ግን መጀመሪያ ከወደደው ውድ
ይልቅ በኋላ የሚጠላው ጥል ይበልጣል! ይህን
የመሰለው ፍቅር በመፅሐፍ ቅዱስ የአምኖን
ፍቅር /አምኖናዊ ፍቅር/ ይባላል።
/3/ “ሎጂካል ላቭ” Logical Love
ይህ ፍቅር ጣራና መሰረቱ “መመሳሰል”
የሚለው ቃል ነው። እነዚህ ፍቅረኛሞች
የሚመሩት በሎጂክ ነው። ለምሳሌ እሷ ድግሪ
ካላት የምትመርጠው ድግሪ ያለውን ሰው ነው።
ወንዱም እንደዚሁ።
/4/ “ፍሬንድ ሺፕ” /Casual friendship/
ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም። ሁለቱ
ፍቅረኛሞች ምስጢር ይለዋወጣሉ፣
የሚያስደስታቸውም ጥምረታቸው ብቻ ነው።
/5/ “ፉሊሽ ላቭ” foolish Love
“የጅል ፍቅር” አንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን
የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው። ለምሳሌ
ምንነቱን ሳታውቅ ፎቶውን ብቻ አይታ ከነፍኩ
በረርኩ የምትል ሴት አጋጥሟችሁ አያውቅም?
ፎቶውን ብቻ አይታ ወደደችው! በቃ! ቆረጠች።
በእቴጌ ጣይቱ ጥናት መሰረት ብዙዎች በዚህ
ፍቅር ከተያዙ ቆይተዋል ይባላል። እድሜና ጤና
ለፌስ ቡክ ይሁንና የእቴጌ ጣይቱ ጥናት ፍንትው
ብሎ ያሳየናል። ይህ አይነቱ ፍቅር በምሁራን
አገላለፅ “የጅል ፍቅር” foolish Love
ይባላል።
/6/ “ፖሰሲቭ ላቭ” /possessive Love/
ይህ ዓይነቱ ደግሞ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ
የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ነው። ወንድ
ስለሆንክ ለራስህ አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ጥናቱ
እንደሚያሳየው ብዙውን ጊዜ ይህ አይነት ፍቅር
የሚይዛቸው ሴቶች ናቸው። እንደዚህ ዓይነቶቹ
የእገሌ ባል መባልን ይፈልጋሉ። /7/
“አንሰልፊሽ ላቭ” unselfish Love
ይህ እሷ ከምትጎዳ እኔው ልቸገር ዓይነት ፍቅር
ነው። ፍቅር ግን መዋደድ እንጂ ውለታ
መዋዋል አይደለም።
/8/ “ጌም ፕሌይንግ ላቭ” Game playing
Love
ይህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ዓላማቸው አንድ
ብቻ ነው። የሩካቤ ሥጋ ጥማቸውን ማርካት
ብቻ። ይህ ብዙውን ጊዜ በወንዶች የሚበረታ
የፍቅር ዓይነት ነው።
/9/ “ኢምፒቲ ላቭ” Empty Love
ባዶ ፍቅር! ይህ ዓይነቱ ፍቅር በአጋጣሚ
ተገናይተው ወደድኩሽ ፣ ከነፍኩልሽ ፣ አበድኩልህ
፣ ክንፍንፍ አልኩልህ የሚያሰኘው ነው።
/10/ “ሰልፊሽ ላቭ” selfish Love
ራስ ወዳድ ፍቅር! እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርን
“ሀ” ብለው የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር
ለማግኘት ነው። ለዚህኛው ፍቅር መሰረቱ
ገንዘብ ነው። “ገንዘብ ያልቃል ፍቅር ግን
ይዘልቃል!” ገንዘቡ እስካለ ድረስ ሆዴ! አንጀቴ!
ሞትኩልህ! አበድኩልሽ! ይባባላሉ። ገንዘቡ
የጠፋ ዕለትስ? ያኔማ ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ
ዓይናቸውንም አያሹም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ
የምትሆነን የኢዮብ ሚስት ናት። ኢዮብ ሐብት
ንብረቱ ሲያልቅ የሚስቱ ፍቅርም አለቀ፤ ኧረ
እንዲያው ለመሆኑ ፍቅር በአንድ ጊዜ የሚለቅ
የጥፍር ቀለም ነው እንዴ? ይህ ዓይነቱ ፍቅር
ገንዘቡ ሲጠፋ ፍቅሩም ድርግም የሚል
“የኢዮባዊ ሚስት ፍቅር” ይባላል።
/11/ “ኮምፓኒየን ላቭ” companion Love
ይህ እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጪ ወጣ
ያለባቸው ሰዎች የሚጀምሩት ውጥን ነው።
ከእድሜያቸው ጋር ግብግብ ስለሚይዙ ያገኙትን
አጋጣሚ ተጠቅመው ያገባሉ። ምክንያቱም
ፊታቸው ያለው የልጅ አምሮት ፣ ልጅ ማሳደግ
አብሮ መኖር …… ነው። እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ
ትዳራዊ ፍቅር companion Love ይባላል።
/12/ † ፍቅር …. እስከ …. መቃብር †
“ኮንሲዮሜት ላቭ” consummate Love
ይህ ዘለቄታ ያለው የአባ ወራ እና የእማ
ወራዎቻችን ፍቅር ነው። ይህ ክቡር አዲስ
አለማየው እንደደረሱት “ፍቅር እስከ መቃብር”
እንደ በዛብህና ሰብለ ወንጌል ያለ ፍቅር ነው።
ይህ የሽማግሌው የአቶ ዘካርያስ እና የወ/ሮ
ልቤነሽ “ፍቅር እስከ መቃብር” ነው! ይህ
“እውነተኛ ፍቅር ነው!!
ፍቅርን ፍቅር ነው የሚያሰኙት 3 ነገሮች ሲሟሉ
ነው።
ስሜት /passion/ ቅርበት /intimacy/
ቁርጠኝነት Commitment
“መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!”
እንዲሉ መግባባት ያስፈልጋል። ሁለቱ
ፍቅረኛሞች በስሜትና በአስተሳሰብ መግባባት
አለባቸው። በአስተሳሰብ መቀራረብ ያስፈልጋል።
በችግርና በኀዘን ለመረዳዳት ቁርጠኝነትም
ያስፈልጋል።ራስን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ማንም
ራሱን ፈልጎ ማግኘት አለበት! እኛ የቱ ጋ ነው
ያለነው?

Thursday, April 11, 2013

ወይ ቆንጅየዋ ልጅ- ውበትሽ ያማረ
ያልተማረው ልቤ-አንቺን ባፈቀረ
‹መሃይም!› ነው ብለሽ-
ትሰድቢኝ ጀመረ
አበጀሁ!
እንኳን መሃይም ሆንኩ፤
ሥራዬ ፍቅር ነው፣
ፊርማ ማይጠይቀኝ…
የተማረ ብሆን…ፊደል የቆጠረ…
ውሎዬ ታንቺ ጋር…መች ይሆን ነበረ
አንቺዬ....
ስስምሽ ስላደርኩ ትላንትና በህልሜ
ዛሬን ቶሎ ተኛው ልስምሽ ደግሜ
የህልሜ ደራሲ አትታደል ቢለኝ
ህልሜን ገለባብጦ ሲስሙሽ አሳየኝ




እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት::
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ
ማንም በምንም ሊከፍለው አይችልምና
ከመሞቷ በፊት የሚገባትን ክብር እንስጣት::
እስታውስ:ሁላችንም አንድ እናት ነው ያለችን::


እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት::
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ
ማንም በምንም ሊከፍለው አይችልምና
ከመሞቷ በፊት የሚገባትን ክብር እንስጣት::
እስታውስ:ሁላችንም አንድ እናት ነው ያለችን::
Add caption

Tuesday, April 9, 2013

ስሚ...Aster ........
አምና ካችአምና
መውደድሽ አስክሮኝ
ፍቅርሽም አውሮኝ
የፃፍኩሌሽ ግጥም
የፃፍኩልሽ ቅኔ
አሁን ግን ሳነበው
አይመስለኝም የኔ
ውዴ አትቀየሚኝ
እውነቱን ልንገርሽ
ጨረቃን አይመስልም
በፍፁም ውበትሽ
የፊትሽ በርሃን
ከፀሀይ አይበልጥም
ገላሽ ልስላሴው
ብዙም አይመስጥም
በፊት ያልኩሽ ሁሉ
ዛሬ ላይ ሳስበው
ችግሩ የአየኔና ያተያየቴ ነው
በሞገስ ጋሻው12-6-2005
ለጋ ጥንቅሽ ነች ጥሬ ከቶ ያልበሠለች
ፅዱ የምንጭ ማር ወታ ያልፈለቀች
በመል ከፀባይ ከሰቶች የመጠቀች
ከእንቁ ከአልማዝ ከፈርጥ የከበረች
የወይን ፍሬ የቴምር አበባ እንቡጥ ፅጌረዳ ሆድን የምታባባ
የፍቅር ቡቃያ የትግስት ዘንባባ
የደም ገንቦዬ ነች የፍቅር ወለባ
የጌት ልጅ ነች ያደላት ፀባየ ሸጋ
አለማዊ መኖክሴ ናሪ በደጋ የሰላም እርግብ ተጋዥ ፍቅርን ፍለገ
ያበሻ ደም የጠይም አገልግል
የጀግና ዘር የሶታዎች ሁሉ ገድል
የሴት መልአክ የዕንስቶች ጀንበር
የፍቅር ማምለኪያ የሁሉም ደብር
ይድረስ ላንቺ ካለሽበት ስፍራ
ሻጊዝ አዶናይ ነኝ ካለሁበት ቦታ


"ቋሚ ተሰላፊ"

በገዘፈ ቢሆን
ተፈጥሮ አሸናፊ
ዳይኖሰር ነበረ
ቋሚ ተሰላፊ
By:ቶማስ ወልዴ

"ጥርሴም...."

ጥርሶች የሌላቸው
አዛውንት አግኝቼ
ምን ሆነው ነው አባት
አልኩኝ ተጠግቼ
እንደዚህ ነው ልጄ
ፈገግ እያሉልኝ
የጥጋቡ ጊዜ
ያኔ ልጅ ሳለሁኝ
ድዴ አልበቃ ብሎ
ድርብ ጥርስ ነበረኝ
የኋላ ኋላ ግን
ዘመኑ ሲገፋ
እህሉን አየና
ጥርሴም አብሮ ጠፋ
ቶማስ ወልዴ,1997

Friday, April 5, 2013



                                                        ኢትዮጵያ ተደፍራ ምኒሊክ ቢቆጣ፣
በጊዮርጊስ ሰይፍ ጣሊያን ተቀጣ።

አሉላ ፈረስህን ልጓሙን አትንካ፣
ከቀይ ባሕር ደርሶ ጥሙን ሳያረካ።

አሉላ ፈረስ ግልቢያ ማነው ያስተማረህ
ባንድ ጀንበር ሽምጥ ኤርትራን ያካለልህ።

(የአማርኛ መወድስ ለሙከራ፤ ኤፍሬም እሸቴ፤ የካቲት 23/2005 ዓ.ም፤ ማርች 2/2013፤ ሀገረ ማርያም፣ ሜሪላንድ)

“ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ፣
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ።”
(አገርኛ ሥነ ግጥም)