Sunday, March 31, 2013


ሀገሬ እሪበይ
ሀገሬ እሪበይ አልቅሺ ደም እንባ
የማህፀንሽ ፍሬ ሲሆን ሌባ ገብጋባ
ልበ’ ገለባ
ሀገሬ አልቅሺ ኡኡ በይ
የሚያስብሽ የለምና ውበትሽን የሚያይ
ደም እንባ ይውጣሽ አልቅሺ ሃገሬ
ፍትህ ተቆራርጦ ሰው ተቆጥሮ እንደበሬ፤
ጥንድ ጥንድ አደርገው አሸክመው ቀንበር
ያርሱበታል እና ያን ደሃ ገራገር
ግድ የለሽም አልቅሺ ላምላክሽ ንገሪው
እንዳለ መፅሐፉ እጆችሽን ስጭው፡፡
/ካሌብ ብርሃኑ






ትርጓሜ

<አስቀያሚ፣
አስጠሊታ፣
መልከ ጥፉ፣
እንደ ደሃ ቀዬ መስህቦችህ የረገፉ፣
የማትባል እዚህ ግባ፣
የሰው ፍራሽ፣ማማር አልባ፣
ፊተ‐መዓት ፣ያ‘መድ ክምር፣
የጭራቅ ሳቅ፣ያ‘ይጥ ድምር፣
ባትታይም የማታምር!>

ኧረ! ሌላም፣ሌላም፣ 
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ፣
አቤት ሃሴት፣አቤት ደስታ።

ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሸ የማይሸር ጥላቻ፣
ደስታ አሰከረኝ ስላየሺኝ ብቻ።

በረከት በላይነህ






ጥርሴም...."

ጥርሶች የሌላቸው
አዛውንት አግኝቼ
ምን ሆነው ነው አባት
አልኩኝ ተጠግቼ
እንደዚህ ነው ልጄ
ፈገግ እያሉልኝ
የጥጋቡ ጊዜ
ያኔ ልጅ ሳለሁኝ
ድዴ አልበቃ ብሎ
ድርብ ጥርስ ነበረኝ
የኋላ ኋላ ግን
ዘመኑ ሲገፋ
እህሉን አየና
ጥርሴም አብሮ ጠፋ

ቶማስ ወልዴ,1997


No comments:

Post a Comment