Sunday, March 31, 2013
ካነበብኩአቸው by Asefafaw
"ላንቺ..."
ቃላቶች ያጥሩኛል ብዬ
ሽንገላን አላስቀድምም
ታውቂያለሽ ቃላቶች ከእኔ
በፍፁም ጠፍተው አያውቁም
ይልቅ ድምፃቸው ሸሽቶ
ሲያንሱ ሲዋጡ ገርሞኛል
ስለፀባይ ውበትሽ ልናገር
ላንቺ ድምፆች ያጥሩኛል
ቃላቶች ያጥሩኛል ብዬ
ሽንገላን አላስቀድምም
ታውቂያለሽ ቃላቶች ከእኔ
በፍፁም ጠፍተው አያውቁም
ይልቅ ድምፃቸው ሸሽቶ
ሲያንሱ ሲዋጡ ገርሞኛል
ስለፀባይ ውበትሽ ልናገር
ላንቺ ድምፆች ያጥሩኛል
ቢኖረኝ መኪነ
ሴቶቹን በሙሉ
ሰልፍ አሰልፍና
ትቻቸው አሄዳለው
ጠበቁኝ እልና
በሞገስ ጋሻው16-6-2005
ፈራጅና ዳኛ '
ቁንጫና ትኋን ፉክክር ገቡና
ያለቁና ሰፍረው ደሜን መጠጡና
በተለይ ቁንጫ ትኋን መሆን አምሯት
ሲያዘልል ሲያፈርጣት
መዥገር ነበር አሉ ታዛቢና ዳኛ
ግን ምን ያደርጋል መዥገርም እንደዛው
ከደም መጣጭ ጋራ ተሰልፎ ኖሮ
ማን ለማን ይፈርዳል ፍርድ የለም ዘንድሮ !!!ውጭ ሀገር --- ዶ/ር ፍቃደ አዘዘ
----------
ብቸኝነት ማለት
አንድ ክፍል አንድ ቤት፤
አራት ግድግዳ
እውስጧ ጠባብ አልጋ፤
አይምሰልህ ልጄ!
ነውና ብቸኛ የረገፈ ቅጠል፣
ከባህሉ ውጪ ከድንበሩ ከለል፡፡
1971
ዶ/ር ፍቃደ አዘዘ
አንድ የኳስ ሱሰኛ የሆነ ወዳጄን እንዴት ነህ ባያሌው ቢዬ ስጠይቀው ምን ብሎ ቢመልስ ደስ ይላችኋል ወጪዬ እና ገቢዬ እንደማድሪድ እና ባርሳ ነጥብ ተራርቆ የወር ደሞዜ እንደ አርሰናል ዋንጫ እየናፈቀቺኝ ንሮ ሚሉት ነገር እንደጣሊያን ሴሪያ ካቴና ሰርቶብኝ እንደሞሪኒሆ እየተኩራራሁ እንደ ማንቺኒ እየተናቆርኩ ልክ እንደ ሊቨርፑል ደጋፊ በሙሉ ተስፍ you are never walk alone እያልኩ በመታገል ላይ ነኝ ብሎኝ እርፍ
አትለከፍ ነው መቼም ግን እናንተስ ባያሌው እንዴት ናችሁልኝ
ሀገሬ እሪበይ
፤
ሀገሬ እሪበይ አልቅሺ ደም እንባ
የማህፀንሽ ፍሬ ሲሆን ሌባ ገብጋባ
ልበ’ ገለባ
ሀገሬ አልቅሺ ኡኡ በይ
የሚያስብሽ የለምና ውበትሽን የሚያይ
ደም እንባ ይውጣሽ አልቅሺ ሃገሬ
ፍትህ ተቆራርጦ ሰው ተቆጥሮ እንደበሬ፤
ጥንድ ጥንድ አደርገው አሸክመው ቀንበር
ያርሱበታል እና ያን ደሃ ገራገር
ግድ የለሽም አልቅሺ ላምላክሽ ንገሪው
እንዳለ መፅሐፉ እጆችሽን ስጭው፡፡
/ካሌብ ብርሃኑ
ትርጓሜ
<አስቀያሚ፣
አስጠሊታ፣
መልከ ጥፉ፣
እንደ ደሃ ቀዬ መስህቦችህ የረገፉ፣
የማትባል እዚህ ግባ፣
የሰው ፍራሽ፣ማማር አልባ፣
ፊተ‐መዓት ፣ያ‘መድ ክምር፣
የጭራቅ ሳቅ፣ያ‘ይጥ ድምር፣
ባትታይም የማታምር!>
ኧረ! ሌላም፣ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ፣
አቤት ሃሴት፣አቤት ደስታ።
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሸ የማይሸር ጥላቻ፣
ደስታ አሰከረኝ ስላየሺኝ ብቻ።
በረከት በላይነህ
ጥርሴም...."
ጥርሶች የሌላቸው
አዛውንት አግኝቼ
ምን ሆነው ነው አባት
አልኩኝ ተጠግቼ
እንደዚህ ነው ልጄ
ፈገግ እያሉልኝ
የጥጋቡ ጊዜ
ያኔ ልጅ ሳለሁኝ
ድዴ አልበቃ ብሎ
ድርብ ጥርስ ነበረኝ
የኋላ ኋላ ግን
ዘመኑ ሲገፋ
እህሉን አየና
ጥርሴም አብሮ ጠፋ
ቶማስ ወልዴ,1997
ጥርሶች የሌላቸው
አዛውንት አግኝቼ
ምን ሆነው ነው አባት
አልኩኝ ተጠግቼ
እንደዚህ ነው ልጄ
ፈገግ እያሉልኝ
የጥጋቡ ጊዜ
ያኔ ልጅ ሳለሁኝ
ድዴ አልበቃ ብሎ
ድርብ ጥርስ ነበረኝ
የኋላ ኋላ ግን
ዘመኑ ሲገፋ
እህሉን አየና
ጥርሴም አብሮ ጠፋ
ቶማስ ወልዴ,1997
Thursday, March 28, 2013
Subscribe to:
Posts (Atom)