Friday, February 15, 2013

“መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።” 
የማቴዎስ ወንጌል 22/ 29
 
 



ይህ አምልኮ ነው ወይስ ሐዘን? ወደ የት አያመራን እንደሆን እናስብበት!! ሲጀመር ይህ ሀዘን በዛ ብለን ነበር ፤ መጨረሻው ይህ ሆኖ አረፈው ፤ በማን ይፈረዳል? ሀዘንም ይሁን ደስታ መጠኑን ማለፍ የለበትም ፤ ሁላችንም ሟች ነን ፤ በህይወት ለሚለየን ሰው አግባብ ባለው መንገድ ሀዘናችንን መግለጽ ይገባል ፤ ነገር ግን መስመር ከሳተ አደጋ አለው ፤ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴዎቹ ይህ ይመጣል ብለው ላያስቡ ይችላሉ ፤ የመጀመሪያው ፎቶ ላይ ስትሰግድ የምትታየው በአስራዎቹ የምትገኝ ልጅ ናት ፤ ሁለተኛው ደግሞ ጎልማሳ ነው ፤ ይህንስ ምን ይሉታል ፤ ቤተክርስትያን ለጸሎት የማይነሳ እጅ ቤተመንግስ እንዲህ ተነስቷል  


ሰዎ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  ጥሩ ከሚባሉ የአፍሪካ መሪዎች ግንባር ቀደም ናቸው ይላሉ፤ አሁን እግዚአብሔር ፈቅዶ  በሞት ተለይተውናል ፤  እሳቸውን የመመለስ አቅም የሌለውን እንባ ከምናፈስላቸው ይልቅ ሀገራችን ቅን ፤ አስተዋይ ፤ አርቆ አሳቢ ፤ ህዝብን የሚያከብር ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ፤ ችግሮችንን የሚፈታ ፤ ማስተዋልና ጥበብን ተሰጠው መሪ እንዲሰጠን ብንጸልይ መልካም ነው፡



 posted by asefafaw on fabruary 08/2005 E.c.